ካልተከሰሰበት ወይም ማዕቀብ ካልተጣለብት ሕጋዊ ማዕቀፍ መደርደሩ ብቻ ግብ አይደለም።

 

—የአዲስ አበባ ራስ ገዝ አስተዳደር(Chartered City) በህዝብ ቁጥር ከሚበልጡት ክልሎች ሁሉ ከፍተኛውን የግብር ገቢ ይሰበስባል ፤ ነገር ግን አብዛኛውን ጠራርጎ ለስርዓቱ ያስገባል። በጤና አገልግሎት ዕጥረት ፣ በአካባቢ ንፅህና ፣ በድህነት ፣ በሱስ ፣ በድብርት ፣ በስደትና በሌሎች ውስብስብ ችግሮች ረገድ መገናኛ ብዙሃን ባይሸፍኑለትም አዲስ አበባ ፩ኛ ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት የወያኔ ስርዐት ትግራይን ያለማውና በአዲስ አበባ ያሉትን <ልዋጭ ልዋጮቹን> ያከበረው መጀመሪያ በአዲስ አበባ ህዝብ ስቃይ(ግብር) ነው። ለአበይትነት ከትንሽ ነገር ተነስታ ሆቴል የከፈተችውን የኔን ውድ አክስት በከፍተኛ ግብር የተነሳ ልብ ድካም ሲገድል የራሱን <ልዋጭ ልዋጮቹን> በአንድ ጀምበር አስከብሯል።
—በህዝብ ቁጥር አዲስ አበባ ከትግራይ በ፴(30%) ቢበልጥም የአዲስ አበባ ህዝብ በኢህአዲግ ማዕከላዊ ኮሚቴና በላይኛው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምንም ተወካይ እንዳይኖረው ተደርጎ ህገ መንግስቱ (ይቅርታ ህገ አራዊቱ) ፀድቆበታል። ከዚህ በፊት እምለውን ነገር እንሆ እደግመዋለው <<ህገ አራዊቱ ሲወጣ ሆን ተብሎ ዐማራን ፣ ጉራጌን ፣ ቅይጥ ብሄሮችን ፣ የአዲስ አበባን ነዋሪና በተለያዩ ክልል ያሉ የዐማርኛ ተናገሪዎችን ለማደን በሚያስችል ‘አግላይ ማዕቀፋዊ ስልትን' ማዕከል ባደረገ መልኩ ነበር። ባለፉት ፪፯ ዓመታትም ያየነው እነዚህን ዕኩይ ህጎች የማስፈፀም ወንጀል ነው።>>
አብይ የአዲስ አበባን ህዝብ ሳያነጋግር እንደተለመደው በሚሊኒየም አዳራሽ የክልል ልጆችን ሰብስቦ እራሱን ሰለብሪቲ ለማስመሰል እየሞከረ እንደሆነ ከክልል የወጣቶች አመራር ሊጎች የሚወጡ የሽርጉድ መረጃዎች ያመላክታሉ። 
አሁን ባሉ የዓለማቀፍ ህጎች አማካኝነትም የስርዓቱን <አግላይ ማዕቀፋዊ ስልትን> በሆላንድ በሚገኘው የዓለም አቀፍ ፍርድቤት ሊያስከስሱ የሚችሉ ከበቂ በላይ ህጋዊ ማዕቀፎች አሉ። በዚህም ረገድ ከሚመለከታቸው አካልት ጋር ለመስራት ዝግጁ ነኝ።  
ባሉ የዓለም ህጋዊ ማዕቀፎች ስርዐቱን ሳንከስ ወይም ስርዐቱ ላይ ማዕቀብ ሳናስጥል በአዲሱ H.Res 128 በተሰኘው ህጋዊ ማዕቀፍ መደሰት ብቻውን በቂ አይደለም። ብዙ ያልተጠቀምናቸው ንዑስ ህጋዊ አስተዋፆዎች አሉ።   

By Mikael Arage 

 

የእርስዎ አስተያየት ይለጥፉ

አስተያየቶች

አስተያየት ለመስጠት የመጀምርያ ይሁኑ

ተዛማች ፅሁፎች